Showing posts with label Getachew Reda. Show all posts
Showing posts with label Getachew Reda. Show all posts

Wednesday, November 10, 2021

ጀግናው የትግራይ ሠራዊት ከኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ጋር በመተባበር በፋሽስት ቡድን በከሚሴ ከተማ ታስረው የነበሩ 55 የትግራይ ተወላጆች ነፃ አወጣ፡

 ጀግናው የትግራይ ሠራዊት ከኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ጋር በመተባበር በፋሽስት ቡድን በከሚሴ ከተማ ታስረው የነበሩ 55 የትግራይ ተወላጆች ነፃ አወጣ፡



-*************************************

እስረኞች በእስር ቆይታቸው ከፍተኛ ግፍና ስቃይ እንደደረሰባቸውም ተናግረዋል፡፡ 

በአውደ ውግያ ከፍተኛ ሽንፈት እየተከናነበ ያለው የፋሽስቱ ቡድን የትግራይ ተወላጆችን ማሰርና ማሳደድ የእለት ተእለት ስራው አድርጎታል፡፡


ፋሽስቱ በደሴ እና አካባቢው ለበርካታ አመታት ይኖሩ የነበሩ 55 የትግራይ ተወላጆች ትግራዋይ በመሆናቸው ብቻ ከሶስት ወራት በላይ አስሯቸዋል፡፡ 

ጀግናው የትግራይ ሠራዊት ደሴን ሲቆጣጠር ቁስለኛውንና ሬሳውን ማንሳት ያልቻለው የፋሽስቱ ሠራዊት የትግራይ ተወላጆችን በጅምላ ለመግደል ወደ ከሚሴ ከተማ ይዛቸው ፈረጠጠ፡፡ 


የትግራይ ሠራዊት ከኦሮሞ ነፃናት ሠራዊት ጋር በመሆን ሞታቸውን ሲጠባበቁ የነቡሩት የትግራይ ተወላጆች ጥበብ በተሞላበት መንገድ እስረኞቹን ካለ ምንም ጉዳት ማስፈታት ችለዋል፡፡


በንግድ ስራ ላይ ተሰማርተው የነበሩ አቶ መሓሪ ወልደገብርኤል፣ አቶ ግደይ ገብረዝጌአብሄር እና በመንገድ ስራ ፕሮጀክት ተሰማርቶ የነበሩት አቶ ዮናስ ተስፋይ ከታሳሪዎች መካከል ሲሆኑ የፋሽስቱ ሠራዊት ለህወሓት በገንዘብ ትደግፋላችው በማለት ንብረታቸው ዘርፎ በርካታ ግፍና ስቃይ እንዳደረሰባቸው ነው የሚገልጹት፡፡ 


በፋሽስቱ ቡድን ልንረሸን ቀናችን እየተጠባበቅን በነበርንበት ጊዜ የትግራይ ሠራዊት እና የኦሮሞ ነፃናት ሠራዊት ጥረት በህይወት እንድንተርፍ አድርጎናል ብለዋል፡፡

በይብራህ እምባየ

Tuesday, November 9, 2021

ከትግራይ መንግስት የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ!


ከትግራይ መንግስት የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ!

ህዝብ ከህዝብ ደም ለማቃባት የተሸረበው ሴራ፣ ለማክሸፍ እንረባረብ!!

ከትግራይ መንግስት የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ!
ህዝብ ከህዝብ ደም ለማቃባት የተሸረበው ሴራ፣ ለማክሸፍ እንረባረብ!!


በኢትዮዽያ ያለው ሁኔታ፣ በዋነኛነት ወራሪ ሃይሎች በቅንጅት፣ በትግራይ ህዝብ ላይ ያካሄዱትና እያካሄዱት ያለውን የዘር ማጥፋት ያስከተለው ሁለንተናዊ ቀውስ ባለፉዉ አንድ አመት በአየር እና በምድር፣ የትግራይ ህዝብ በጅምላ በመጨፍጨፍ፣ በጥይት፣ በገጀራና በድንጋይ ወግረው በመግደል፣ የንፁሃን ወገኖቻችን አስከሬን ነዳጅ አርከፍክፈው በማቃጠል፣ ከእነ ነብሳቸው ወደ ሽንት ቤት እና ገደል በመወርወር በታሪክ ይቅር የማይባል አረመንያዊ ተግባር በመፈፀምና አሁንም ያደረጉት እኩይ ተግባራቸው አጠናክረው እንደሚቀጥሉበትም ከመዛት አልፈው በተግባር የትግራይ ተወላጆች በገፍ እየታሰሩና እየተገደሉ ይገኛሉ።

በመሆኑም ባለፉዉ አንድ አመት ፖለቲካዊ፣ ወታደራዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ሽንፈት የተከናነበው የፋሽሽት አብይ አሕመድ ቡድን እና ተስፋፊዉ የአማራ ክልል መንግስት በአሁኑ ወቅት አገሪትዋ በማትወጣበት አዘቅት አስገብቶዉ፣ መቀመቅ ከወረድዋት በኋላ፣ እንደ ለመዱት የተለያዩ የውሸት ድራማዎች ፈጥረው፣ በመደበኛ ሰራዊታቸዉ የደረሰዉን እልቂት አልበቃ ብሏቸዉ በተለያዩ አወደ ውግያዎች እንዳልነበረ ከተበታተነና ከፈረሰ በኋላ ለየት ባለ የታምቡር አታሞና ቃና፣ የታጀበ ወደ ህዝባዊ ጦርነት እንቀይረዉ በሚል ፈሊጥ የአማራ ህዝብ ከትግራይ ህዝብና ሰራዊት ደም ለማቃባት የቅጥፈት መዝሙር ሲዘምሩ ሰንብቷል፡፡

ይህንን ሁሉ ልክ ያጣ የቀን ቅዠት ቀረርቶ የሚያሰሙት የፋሽሽት አብይ አሕመድ ቡድን እና ተስፋፊዉ የአማራ ክልል መንግስት ቅጥረኛ ሰራዊትና ታጣቂ ሐይሉ፣ በትግራይ ሰራዊት ተደምስሶበት ሰራዊቱ በመፍረሱ እና የስልጣን ወንበራቸዉ በተነቃነቀበት የነዚህ አረመኔ ቡድኖች በውሸት ፕሮፖጋንዳ የቀቢፀ ተስፋ፣ አንዴ የህልዉና ዘመቻ፣ በሌላ ክተት ወደ ጦር ግንባር እያሉ ፀሃያቸዉ በጠለቀችበት ወቅትና ግዜም ሳይቀር ህዝቡን በማደናገር የአማራ ህዝብ ለማስፈጀት እየዳከሩ ይገኛሉ። ይሁን እንጂ የትግራይ ህዝብ፣ ሰራዊት እንዲሁም መንግስት ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ እንደገለፁት ከአማራ ህዝብ የጥቅምም ይሁን የሌላ ግጭት እንደሌለዉ መላዉ የአማራ ህዝብ በዉል ሊያውቅ ይገባል፡፡

ሰለሆነም የትግራይ ህዝብ፣ እና ሰራዊት አንድነቱ ይበልጥ እንደ ብረት አጠናክሮ በሚፈልጋቸው ቦታዎች እና ጊዚያቶች፣ ደመኛ ጠላቶቹን ፋሽስት ስርአቱን ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ለመቅበር በሚያደርጉት ትግል የበኩላቹህ አስተዋፅኦ እንድታበረክቱና በአማራ ህዝብ ሂወትና ደም የስልጣን ዘመናቸዉ ለማራዘም እየተፍጨረጨሩ ያሉት የወንጀሎኞች ሴራ እንድታከሽፉ የትግራይ ህዝብና መንግስት በአፅንኦት ጥሪዉን ያስተላልፋል፡፡

በመጨረሻም ሁሉም ወራሪ ሃይሎች፣ ሲቪል ባለስልጣናት፣ ወታደራዊ መኮንኖች፣ የወረራው ቀያሾች እና አመራር ሰጪ አካላት፣በአጠቃላይ ሁሉ የጥፋት ተዋናዮች፣ በጦር ወንጀለኝነት ተከሰው በአገርና በአለም አቀፍ የፍትህ መድረክ ተገቢው ፍርድ የሚሰጥባቸዉ ቀን ሩቅ እንዳልሆነ ተገንዝባቹሁ ሁላችሁም የሚመለከታቹህ አካላት ከዚህ እኩይ ተግባር ራሳቹ እንድታገሉ እያሳሰብን ይህን ሳይሆን ሲቀር ግን ለሚደርሰዉ ኪሳራና እልቂት ተጠያቂዉ ቀን ተሌሊት ህዝብ ለማስፈጀት ክተት ወደ ጦር ግንባር በማለት እያላዘኑ ያሉት የጦር ወንጀለኞቹ ፋሽስት ቡድን አብይ አሕመድና ተስፋፊዉ የአማራ ክልል መንግስትና ሁሉም ተባባሪዎች መሆናቸዉ ወዳጅም ጠላትም በዉል ሊያዉቅ ይገባል፡፡ 

የትግራይ መንግስት
ጥቅምት 30/2014 ዓ.ም

መቐለ 

Saturday, November 6, 2021

Tuesday, November 2, 2021

የትግራይ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በወቅታዊ ጉዳይ ላይ አስመልክተው ያስተላለፉት መልእክት *******


የትግራይ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በወቅታዊ ጉዳይ ላይ አስመልክተው ያስተላለፉት መልእክት  ******** 


“አሁን ከፊት ለፊታችን ያለው ብቸኛ አማራጭ የሰላም ጥሪ የረገጠው ፋሽስታዊ ቡድንን በመደምሰስ ህዝባዊ ምከታችን በአንፀባራቂ ድል ማጠናቀቅ ብቻ ነው!” --- የትግራይ ህዝብ በረጅም የታሪክና የነፃነት ገድል ታሪኩ ህልውናውንና ደህንነቱን ከማስከበር፣ ታሪኩንና ማንነቱን ጠብቆ ከማቆየትና እንደዚሁም የግዛት አንድነቱን ከማረጋገጥ፣ ከድህነትና ኋላቀርነት አረንቋ ለመላቀቅ ተገዶ የገባበት ካልሆነ በቀር፤ የሌሎች ህዝቦች መብት ለመርገጥ አልያም ለመውረር ዓልሞ ያካሄደው ጦርነት ፈፅሞ አልነበረም።  ስለሆነም የትግራይ ህዝብ በራሱ ላይ በተፈፀሙበት ቀጣይ ወረራዎች ምክንያት በየምዕራፉ ለህልውናው፣ ለመብቱና ለማንነቱ ሲል ተወዳዳሪ የሌለው ትግል አካሂዷል። በአካሄደው መራራ ትግልና በከፈለው ከባድ መስዋእትነት ደግሞ ለማንም ሳይንበረከክ ታሪኩ፣ ክብሩና ማንነቱ ሳይበረዝ ጠብቆ እንደቆየ ሁሉ ዛሬም ነፃነቱንና ክብሩን አስጠብቆ መቀጠል ችሏል። ማንነቱንና ታሪኩን ለማስቀጠል የቻለው ደግሞ በቀና ጎዳና ላይ ተጉዞ ሳይሆን እጅግ ከባድ፣ መራራና ፈታኝ መድረኮች፣ አያሌ ውስብስብ ችግሮችን በጥበብ፣ በጥንቃቄና በብቃት መሻገር በመቻሉና እያንዳንዱ ትውልድም በራሱ የግዜ መዋዕል መድረኩ የሚጠይቀውን ሁሉም ዓይነት ትግልና መስዋእትነት ስለከፈለ ነው።  በአሁኑ መድረክም ቢሆን ጠላቶቻችን ካለፉት ግዜያቶች በከፋ ደረጃ የትግራይ ህዝብን ተረት ለማድረግ ማለቂያ የሌለው ኮተትና የጥፋት ግብረ-አበሮቻቸውን አሰልፈው ዳግመኛ ግልፅ ወረራ ፈፅመውብናል።   ይሁን እንጂ ጠላቶቻችን እንደ ህዝብ ከምድረ ገፅ ሊያጠፉን ቢዘምቱብንም እንደ ህዝብ አንድነታችንን አጠናክረን በላቀ ፅናትና ብሄራዊ ስሜት በመታገላችን እነሆ ሁሉንም ከበባዎችን በርግደን በመጣስ የጠላቶቻችን ዕድሜ ለማሳጠርና ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ለመቅበር በምንችልበት ደረጃ ላይ ደርሰናል።  ስለሆነም በአሁኑ ሰዓት የትግራይ ህዝብን ዘላቂ ህልውናና ደህንነት በአስተማማኝ ደረጃ ለማረጋገጥና በጠንካራ መሰረት ላይ ለመገንባት በምንችልበት ደረጃ ላይ እንገኛለን። አሁን የትግራይ ሰራዊትን ግስጋሴ ሊያስቆም የሚችል ምድራዊ ሃይል የለም።  አሁን በትግራይ ላይ ያንዣበበው የጥፋት ዳመና ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ተገፎ ወደ አዲስና የተለየ ምዕራፍ የሚያሸጋግር ሰፊ ዕድል ጋህድ እየሆነ ይገኛል። ተወዳዳሪ በሌለው የትውልድ ትግልና መስዋእትነት የተረከብናት ትግራይ ወገባችንን ጠበቅ አድርገን በመታገል ሁሉንም ወራሪዎች በበቃኝ  ዘርረን በመቅበር  እኛም እንዳለፉት ትውልዶች ሁሉ ወደ ቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ ታሪካዊ ሃላፊነት በትከሻችን ላይ ወድቋል።  የዚህ ትውልድም በትከሻው ላይ ያረፈውን ሓላፊነት በላቀ ጀግንነት፣ ቆራጥነትና ክብር የትግራይ ግዛት አንድነትን በማስጠበቅ ወደ ቀጣይ ትውልዶች እንደሚያሸጋግር ለአፍታም ቢሆን አያጠራጥርም።  በዚህ ወቅት ያለው ትውልድ ትግራይንና ህዝቧን ለገበያ ድርድር ማቅረብ ማሰብን ይቅርና  ህልም ማለምም  የሚቻል አይደለም።  በትግል ዘመን መዋእሉ ለፍትሕና አንድነት የታገለው የትግራይ ህዝብ የሰላም ጣዕምና ውድ ዋጋ ከሱ  በላይ የሚያውቀውና የሚፈልገው አካል ከቶ ሊኖር አይችልም።  በትግራይ ህዝብና መንግስት ላይ ሊፈፀምባቸው የማይፈልጉትን ግፍና በደል በሌሎች  ህዝቦች ላይም ሊደርስባቸው አይመኙም። ይሁን እንጂ በሰፊው ህዝባችን ላይ በተለይ ደግሞ በትግራይ ሴቶች ላይ የተፈፀሙ ማለቂያ የሌለው ግፍና በደሎች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የተሳተፉ አካላት ሁሉ በገቡበት ገብተን ፍርዳቸውን እንዲያገኙ ማደረጋችን የግድ ይላል።  የትግራይ ህዝብ እንደ ህዝብ ከምደረ ገፅ ለማጥፋት በታወጀው ጆኖሳይድ የተሳተፉት ሁሉ የእጃቸውን እንደሚያገኙ ሊታወቅ ይገባል። በዚህ ላይ “ይቅር” የሚባል ነገር ሊኖር ፈፅሞ አይችልም።  በአሁኑ ወቅት ወራሪ ሃይሎች የመፈፀም ዓቅማቸው ዝቅተኛ ደረጃ የወረደበት፣ የወራሪ ሃይሎች ፉከራና ማስፈራሪያ ሁሉ መሬት የመንካት ዕድሎች የሰፉበት ከመሆኑም ባሻገር ከሁሉም በላይ ህዝባዊ ሰራዊታችን የመፈፀም ዓቅሙ እጅግ በላቀ ከፍታ ደረጃ ላይ ደርሷል ማለት ይቻላል።   በዚህ ሰዓት ላይ የህዝባችንን ህልውናና ደህንነት በአስተማማኝ አገባብ ለማስጠበቅ ብቻ ሳይሆን ትግራይ ዳግመኛ ልትደፈር ወደማትችልበት ደረጃ ላይ ለማሸጋገር የሚያስችል ተጨባጭ ችሎታ እንዳለን ለወዳጅም ለጠላትም ከወዲሁ ለማሳወቅ እንወዳለን።  በመሆኑም አሁን ፊት ለፊታችን ላይ ያለው ብቸኛ አማራጭ የሰላም ጥሪ የረገጠው ፋሽሽታዊ ብዱንን በመደምሰስ ህዝባዊ ምክታችንን በአንፀባራቂ ድል እንዲጠናቀቅ ማድረግ ብቻ መሆኑ ታውቆ እያንዳንዱ ትግራዋይ ዜግነታዊ ግዴታውን እንዲፈፅም ጥሪየን አቀርባለሁ።  ዘልአለማዊ ክብርና ሞገስ ለጀግኖች የትግራይ ሰማእታት! 

 ሰላም! #ትግራይ_ትስዕር 

Thursday, September 30, 2021

Getachew Reda

Abiy Ahmed’s solution to the worsening humanitarian crisis in Tigray is to declare UN humanitarian Personnel in Addis Persona no Grata. 
Those of you who might’ve thought z guy in Arat Killo would b counseled into sanity must be disappointed. Sad but real.

By, Getachew Reda