 |
ከትግራይ መንግስት የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ!
ህዝብ ከህዝብ ደም ለማቃባት የተሸረበው ሴራ፣ ለማክሸፍ እንረባረብ!! |
ከትግራይ መንግስት የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ!
ህዝብ ከህዝብ ደም ለማቃባት የተሸረበው ሴራ፣ ለማክሸፍ እንረባረብ!!
በኢትዮዽያ ያለው ሁኔታ፣ በዋነኛነት ወራሪ ሃይሎች በቅንጅት፣ በትግራይ ህዝብ ላይ ያካሄዱትና እያካሄዱት ያለውን የዘር ማጥፋት ያስከተለው ሁለንተናዊ ቀውስ ባለፉዉ አንድ አመት በአየር እና በምድር፣ የትግራይ ህዝብ በጅምላ በመጨፍጨፍ፣ በጥይት፣ በገጀራና በድንጋይ ወግረው በመግደል፣ የንፁሃን ወገኖቻችን አስከሬን ነዳጅ አርከፍክፈው በማቃጠል፣ ከእነ ነብሳቸው ወደ ሽንት ቤት እና ገደል በመወርወር በታሪክ ይቅር የማይባል አረመንያዊ ተግባር በመፈፀምና አሁንም ያደረጉት እኩይ ተግባራቸው አጠናክረው እንደሚቀጥሉበትም ከመዛት አልፈው በተግባር የትግራይ ተወላጆች በገፍ እየታሰሩና እየተገደሉ ይገኛሉ።
በመሆኑም ባለፉዉ አንድ አመት ፖለቲካዊ፣ ወታደራዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ሽንፈት የተከናነበው የፋሽሽት አብይ አሕመድ ቡድን እና ተስፋፊዉ የአማራ ክልል መንግስት በአሁኑ ወቅት አገሪትዋ በማትወጣበት አዘቅት አስገብቶዉ፣ መቀመቅ ከወረድዋት በኋላ፣ እንደ ለመዱት የተለያዩ የውሸት ድራማዎች ፈጥረው፣ በመደበኛ ሰራዊታቸዉ የደረሰዉን እልቂት አልበቃ ብሏቸዉ በተለያዩ አወደ ውግያዎች እንዳልነበረ ከተበታተነና ከፈረሰ በኋላ ለየት ባለ የታምቡር አታሞና ቃና፣ የታጀበ ወደ ህዝባዊ ጦርነት እንቀይረዉ በሚል ፈሊጥ የአማራ ህዝብ ከትግራይ ህዝብና ሰራዊት ደም ለማቃባት የቅጥፈት መዝሙር ሲዘምሩ ሰንብቷል፡፡
ይህንን ሁሉ ልክ ያጣ የቀን ቅዠት ቀረርቶ የሚያሰሙት የፋሽሽት አብይ አሕመድ ቡድን እና ተስፋፊዉ የአማራ ክልል መንግስት ቅጥረኛ ሰራዊትና ታጣቂ ሐይሉ፣ በትግራይ ሰራዊት ተደምስሶበት ሰራዊቱ በመፍረሱ እና የስልጣን ወንበራቸዉ በተነቃነቀበት የነዚህ አረመኔ ቡድኖች በውሸት ፕሮፖጋንዳ የቀቢፀ ተስፋ፣ አንዴ የህልዉና ዘመቻ፣ በሌላ ክተት ወደ ጦር ግንባር እያሉ ፀሃያቸዉ በጠለቀችበት ወቅትና ግዜም ሳይቀር ህዝቡን በማደናገር የአማራ ህዝብ ለማስፈጀት እየዳከሩ ይገኛሉ። ይሁን እንጂ የትግራይ ህዝብ፣ ሰራዊት እንዲሁም መንግስት ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ እንደገለፁት ከአማራ ህዝብ የጥቅምም ይሁን የሌላ ግጭት እንደሌለዉ መላዉ የአማራ ህዝብ በዉል ሊያውቅ ይገባል፡፡
ሰለሆነም የትግራይ ህዝብ፣ እና ሰራዊት አንድነቱ ይበልጥ እንደ ብረት አጠናክሮ በሚፈልጋቸው ቦታዎች እና ጊዚያቶች፣ ደመኛ ጠላቶቹን ፋሽስት ስርአቱን ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ለመቅበር በሚያደርጉት ትግል የበኩላቹህ አስተዋፅኦ እንድታበረክቱና በአማራ ህዝብ ሂወትና ደም የስልጣን ዘመናቸዉ ለማራዘም እየተፍጨረጨሩ ያሉት የወንጀሎኞች ሴራ እንድታከሽፉ የትግራይ ህዝብና መንግስት በአፅንኦት ጥሪዉን ያስተላልፋል፡፡
በመጨረሻም ሁሉም ወራሪ ሃይሎች፣ ሲቪል ባለስልጣናት፣ ወታደራዊ መኮንኖች፣ የወረራው ቀያሾች እና አመራር ሰጪ አካላት፣በአጠቃላይ ሁሉ የጥፋት ተዋናዮች፣ በጦር ወንጀለኝነት ተከሰው በአገርና በአለም አቀፍ የፍትህ መድረክ ተገቢው ፍርድ የሚሰጥባቸዉ ቀን ሩቅ እንዳልሆነ ተገንዝባቹሁ ሁላችሁም የሚመለከታቹህ አካላት ከዚህ እኩይ ተግባር ራሳቹ እንድታገሉ እያሳሰብን ይህን ሳይሆን ሲቀር ግን ለሚደርሰዉ ኪሳራና እልቂት ተጠያቂዉ ቀን ተሌሊት ህዝብ ለማስፈጀት ክተት ወደ ጦር ግንባር በማለት እያላዘኑ ያሉት የጦር ወንጀለኞቹ ፋሽስት ቡድን አብይ አሕመድና ተስፋፊዉ የአማራ ክልል መንግስትና ሁሉም ተባባሪዎች መሆናቸዉ ወዳጅም ጠላትም በዉል ሊያዉቅ ይገባል፡፡
የትግራይ መንግስት
ጥቅምት 30/2014 ዓ.ም
መቐለ